የዝቋላን ገዳም እንታደግ!!!
ከገዳሙ ጸሐፊ የደረሰን መረጃ፡- (http://www.eotc-mkidusan.org/site/) “ቃጠሎው ከአቅም በላይ ሆኗል፡፡ መነኮሳቱና ምእመናን በመዳከም ላይ ናቸው፡፡ ከእግዚአብሔር በረከትን የምትሹ ምእመናን ድረሱልን፡፡ እሳቱ በአንድ አቅጣጫ ጠፋ ሲባል በሌላ በኩል እየተነሣ ተሰቃይተናል፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ በመገሥገሥ ላይ ስለሆነ የቅዱስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች፣ ማኅበራት፣ ከዩኒቨርሲቲዎችና የኮሌጅ ተማሪዎች፣ እንዲሁም ምእመናንና ወጣቶች፣ አቅም ያለው ሁሉ እሳቱን ለማጥፋት በተቻላችሁ አቅም ድረሱልን፡፡ መምጣት የማትችሉ በጸሎት አትለዩን በማለት ጥሪ አቅርበዋል፡፡”
የምንችለውን በማገዝ ገዳሙ እና አባቶች መነኮሳትን እንታደግ!!!
በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማዕከል::
Your browser does not support inline frames